Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታሪካዊውን መስቀል አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታሪካዊውን መስቀል አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የመስቀል አደባባይን ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን አስምልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፦ “ባለፉት ጥቂት ወራት በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ያለ መታከት ሲደክሙ በቆዩት ወገኖች እጅግ ተደንቄያለሁ” ብለዋል።

“በመስቀል አደባባይ ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ በዚህኛው ዙር በአጠቃላይ 5 ሺህ ያህል ሠራተኞች እየተሳተፉ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አክለውም “ይህንን ታሪካዊ አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው” ብለዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version