አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2012 በጀት ዓመት 325 ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2012 ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2013 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ ሽፈራወ ተሊላ፥ በ2012 በጀት ዓመት 405 ከተሞችን፣ የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 325 የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
ይህ የሆነውም ከነባሩ ሲስተም ወደ አዲሱ የኢ.አር.ፒ ሲሰተም ለማዞር ረጅም ጊዜ በመወሰዱ ነው ተብሏል።
በ2013 በጀት ዓመትም የደበኞችን ቁጥር በ1 ሚሊዮን ለመጨመር፣ የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ፣ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተደራሸነቱን ከፍ ለማድረግ ይሰራል ነው የተባለው።
እንዲሁም 50 ሺህ የሚሆኑ ስማርት ቆጣሪዎች የትግበራ ስራ እንደሚጀመርም ዋና ስራ አሰፈጻሚው አቶ ሽፈራወ ተሊላ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የተቋሙን ንብረት በተለያዩ ጊዜ የተቋሙ ስራተኛ በመምሰል ዝርፊያ የፈጸሙ ግለሰብች በህግ እየተጠየቁ መሆናቸውን ዋና ስራ አሰፈጻሚው አሰታውቀዋል።
የሰነምግባር ችግር ያለባቸው ሰራተኞች ላይም እርምጃ እየተወሰደ ሲሆን፥ አስተዳደራዊ እርምጃን ጠምሮ 75 በሚሆኑ ሰራተኞችን ከሰራ እስከማሰናበት የደረሰ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቅዋል።
በሲሳይ ጌትነት
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።