አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6 ሚሊየን መድረሱ ተነገረ።
በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6 ሚሊየን 365 ሺህ የደረሰ ሲሆን፥ 183 ሺህ 653 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
3 ሚሊየን 313 ሺህ 861 የሚሆኑት ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው፡፡
በዚህም አሜሪካ ከአለም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ይሁን ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ ከዓለም በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ከአሜሪካ በመቀጠልም በብራዚል፣ ህንድ እና ሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት በብራዚል 3 ሚሊየን 722 ሺህ 4 ሰዎች ተይዘው÷ 117 ሺህ 756 ሰዎች በቫይረሱ ምክያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
እንዲሁም በህንድ 3 ሚሊየን 310 ሺህ 234 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን፥ 60 ሺህ 329 የሚሆኑት ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
በሩሲያም 970 ሺህ 865 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው÷ 16 ሺህ 683 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡
እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃም አሁን በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 24 ሚሊየን 339 ሺህ 123 የደረሰ ሲሆን፥ 16 ሚሊየን 877 ሺህ 167 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።