Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 533 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ18 ሺህ 724 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 533 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለፁት ሚኒስትሯ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 725 ደርሷል፡፡
 
በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 515 ሰዎች ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ 311 ደርሷል፡፡
 
አሁን ላይ 327 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉም ነው የተባለው፡፡
 
በኢትዮጵያ እስካሁን ለ813 ሺህ 410 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 45 ሺህ 221 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
 
ከዚህ ውስጥ 16 ሺህ 311ዱ ሲያገግሙ 28 ሺህ 181 ሰዎች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
Exit mobile version