አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች ቀሪ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተቀጠረ ቢሆንም ከ4ኛ እስከ 9ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ውጤት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዪት ስላልመጣ ለነሃሴ 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።
በችሎቱ የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድ ውጭ ሀገር ከሚገኙት ልጃቸው እና ባለቤታቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ አንድ ጊዜ ብቻ መገናኘታቸውን በመግለፅ በድጋሚ እንዲገናኙ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።