Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮምቦልቻ ከተማ በሆቴል ኢንቨስትመንት ለሚሳተፉ ስድስት ባለሀብቶች የመሬት ርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ስድስት ባለሃብቶች ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን ለመገንባት የመሬት ርክክብ ፈጸሙ፡፡

ባለሃብቶቹ በ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በሚገመት ገንዘብ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎችን ይገነባሉ ተብሏል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ መሬቱ በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ለባለሀብቶቹ መተላለፉን ገልፀዋል።

ይህም ከዚህ ቀደም ባለሃብቶችን ለማስተናገድ የሚፈጥረውን እክል እንደሚቀርፍ አስታውቀዋል፡፡

የሚገነቡት ሆቴሎች ሁሉም ባለአምስት ኮከብ ሲሆኑ እስከ ሦስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ተናግረዋል፡፡

ሆቴሎቹ ሲጠናቀቁ ለ 1 ሺህ 478 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ አብመድ ዘግቧል።

Exit mobile version