አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የጣለ ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ጎርፍ የሶስት ታዳጊወች ህይወት አለፈ።
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው በእንሳሮ ወረዳ ላም ገኖ ቀበሌና አካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በስፍራው የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ19፣16 እና 11 ዓመት ሁለት ወንድና አንድ ሴት ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ሰጠኝ በተባለ ወንዝ በመወሰዳቸው ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
በአካባቢው ነዋሪዎች በተደረገ ፍለጋ የሶስቱም እህትና ወንድማማቾች አስከሬን መገኘቱንም ነው የተናገሩት፡፡
ኮማንደር ተስፋዬ አያይዘውም በክረምት ወቅት ከሚከሰቱ አደጋዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በግርማ ነሲቡ