ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፈረንሳይ የ100 ቢሊየን ዩሮ የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ ይፋ ልታደርግ ነው

By Tibebu Kebede

August 26, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ ይፋ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ መንግስት ምጣኔ ሃብቱን ከገባበት ድቀት ይታደገዋል ያለውን የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ ከሳምንት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ካስቴክስ ገልጸዋል፡፡

የ100 ቢሊየን ዩሮ የኢኮኖሚ ማገገሚያው እቅድ ዝርዝር በፈረንጆቹ የመጀመሪያው መስከረም ወር ይፋ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ካለፈው የፈረንጆቹ አመት የመጨረሻ ሩብ አመት ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ሩብ አመት ቅናሽ ማሳየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህ ሳቢያም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እያሽቆለቆለና ድቀት ላይ እንደሆነ መገለጹም የሚታወስ ነው፡፡

የአሁኑ የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድም ውድቀት ላይ ያለውን የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ለማነቃቃት ያለመ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፣ ሬውተርስ