አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ ስትሆን አሜሪካ እና ሶማሊያ ቀጣዩን ደረጃ መያዛቸውን የንግድ እና ኢንዱስት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ኔዘርላድስ አበባ ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ ፣ ቆዳ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ ብረትና የመሳሰሉትን ከኢትዮጵያ በመቀበል 320 ሺህ 162 የአሜሪካን ዶላር በማስግኘት ቀዳሚ ሀገር ሆናለች ብሏል፡፡
አሜሪካ ደግሞ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቡና ጫማ፣ አበባ፣ የቆዳ ውጤቶችን፣ የቅባት እህሎችን እና ሌሎች ኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልካቸውም ምርቶች በመቀበል 295 ሺህ 809 ዶላር በማስገኘት ሁለተኛ ደረጃ መቀመጧን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
እንዲሁም ሶማሊያ 291 ሺህ 855 ፣ ሳውዲ አረቢያ 214 ሺህ 652፣ ጀርመን 174 ሺህ 283 የአሜሪካን ዶላር በማስገኘት እንደ ቅደም ተከተላቸው ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡