አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡባዊ ብሩንዲ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ የ 15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
በደቡባዊ ብሩንዲ ሮሞኒንግ ግዛት የተፈጸመው ይህ ጥቃት የአካባቢው ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው በጫካ ውስጥ እንዲሸሸጉ እንዳስገደዳቸውም ነው የተነገረው።
በአጎራባች ሀገር ዲሞክራቲክ ሪብሊክ ኮንጎ መሰረቱን ያደረገው የአመጺ ቡድን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን መውሰዱን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ አስታውቋል ።
ታጣቂዎቹ በአካባቢው ያገኙትን ማንኛውንም ሰው ሲያግቱ እንደነበር እና ለወታደሮች ድጋፍ ያደረጉትን ደግሞ መግደላቸውን በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል።
የሀገሪቱ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ÷ ጥቃቱ የተፈፀመው የአካባቢያዊ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ በነበረበት ወቅት መሆኑን እና ያልተጠበቀ ጥቃት እንደነበረ ገልፀዋል።
ጥቃቱም በ2017 በቡርንዲ የተቀሰቀሰውን ብጥብጥ ሸሽተው ወደ ሩዋንዳ የተሰደዱ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም ብለዋል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።