ዓለምአቀፋዊ ዜና

ትራምፕ በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰሱ ሶስተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነዋል

By Tibebu Kebede

December 19, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ደምፅ ሰጠ።

ትናንት ምሽት ዘለግ ያለ ክርክር በጉዳዩ ላይ ያደረገው የሀገሪቱ ኮንግረስ ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም እና የኮንግረሱን ስራ ሆን ብለው በማሰናከል ወንጀሎች በምክር ቤቱ እንዲከሰሱ ድምፅ ሰጥቷል።