አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ተጀምሯል።
“ወቅታዊ ፈተናዎቻችንን በህብረትና በፅናት መክተን ወደ ብልፅግና እንሻገራለን!” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ኮንፈረንስ በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የመክፈቻ ንግግር ተጀምሯል።
በኮንፈረንሱ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ ሚስራ አብደላ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ወርዲ ሐሺም፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሀረሪ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ኮንፈረንሱ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ከሃረር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።