Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1 ሺህ 368 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 19 ሺህ 776 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 368 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
በ24 ሰዓታት ውስጥ የ25 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን 567 ሰዎች አገግመዋል።
 
እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 33 ደርሷል።
 
14 ሺህ 480 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል። ያለፉትን 24 ሰዓታት ጨምሮም በአጠቃላይ 662 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል።
 
በአሁኑ ወቅት 251 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 23 ሺህ 889 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል።
 
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 736 ሺህ 904 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
Exit mobile version