Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚኒስቴሩ በተጠናቀቀው በጀት አመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት አመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ።

ሚኒስቴሩ በበጀት አመቱ 270 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 86 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል።

ከዚህ ውስጥ 128 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ከሃገር ውስጥ ታክስ እንዲሁም 104 ነጥብ 9 ቢሊየን ብሩ ከጉምሩክ የተገኘ ሲሆን ቀሪው ከሎተሪ ገቢ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

ገቢው ካለፈው አመት ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ35 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወይም የ17 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።

ይህ ብልጫም ካለፉት አራት አመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር መሆኑም ተገልጿል።

አፈፃፀሙ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አመታት የተሻለ አፈፃፀም የታየበት መሆኑም ነው የተገለጸው።

ሚኒስቴሩ በተያዘው የ2013 በጀት አመትም 290 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱንም ገልጿል፡፡

በታምሩ ከፈለኝ

Exit mobile version