አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ170 ሺህ አልፏል።
ትናንትናም ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው በ483 ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።
ከዚህ ውስጥ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ እና ሉዊዚያና ቀዳሚውን ቁጥር ይዘዋል ተብሏል።
በሀገሪቱ በዚህ ወቅት የሚጀምረው ጉንፋን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዳያባብሰው ስጋት አሳድሯል።
በሀገሪቱ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ይሕ ቁጥር በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
አሁን ላይም ከሃዋይ ፣ ከሳውዝ ዳኮታ እና ኢሊኖይ ግዛቶች በስተቀር የወረርሽኙ ስርጭት በመቀነስ ላይ መሆኑም ይነገራል።
ምንጭ፡-ሬውተርስ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።