አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ በሩብ ዓመቱ 7 ሚሊየን ስለኮሮና ቫይረስ የተፃፉ ሀሰተኛ መረጃዎች ከገጹ ማጥፋቱን አስታወቀ።
የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው ፌስቡክ በሶሰት ወራት ውስጥ 7 ሚሊየን የሚጠጉ ስለኮሮና ቫይረስ የተሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጥፋቱን ነው ያስታወቀው።
አያይዞም በገፁ ላይ ለተለቀቁ ለ98 ሚሊየን ሀሰተኛ ይዘት ላላቸው ፅሁፎችም ማስጠንቀቂያ መስጠቱንም ነው ያስታወቀው።
ከመረጃዎቹ መካከልም የበሽታ መከላከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል እና ሌሎች የጤና ባለሙዎች አደገኛ ናቸው ያላቸውን የቫይረሱ የመከላከያ መንገዶች ያካተተ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።
ባሳለፍነው ሳምንት ፌስቡክና ትዊተር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የህፃናት የበሽታ መከላከል አቅም ከፍተኛ በመሆኑ ለኮሮና ቫይረስ አይጋለጡም በሚል የተሳሳተ መረጃ አውጥተዋል በማለት በገፃቸው ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ይታወሳል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።