የሀገር ውስጥ ዜና

ፍርድ ቤቱ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር እንዲሰማ በተከላካይ ጠበቃ ተወክለው እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

By Tibebu Kebede

August 12, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በአቶ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩም ላይ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር እንዲሰማ በተከላካይ ጠበቃ ተወክለው እንዲቀርቡ ለነሃሴ 8 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡

ዛሬ ከሰአት በነበረው ችሎት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ አቶ አስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩም ጉዳያቸው በችሎቱ ታይቷል።