አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ።
በዚህ መሰረትም ከቀኑ 8 ሰዓት ከ15 ላይ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ እና አትሌት ብርቄ ሃየሎም ይወዳደራሉ።
በተመሳሳይ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ33 ላይ ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል፡፡
በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳልያ ከወዲሁ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው መሆኑን የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።