የሀገር ውስጥ ዜና

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ ወገኖች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

March 21, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 416 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሣምንት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እነዚህ ወገኖች ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በሳምንቱ ውስጥ በተደረጉ ዘጠኝ በረራዎች መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከተመለሱት መካከልም 2 ሺህ 859 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3 ቀን  2017 በይፋ መጀመሩን መረጃው አስታውሷል፡፡

ይህን ተከትሎም እስከ አሁን 3 ሺህ 416 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡