የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

By Hailemaryam Tegegn

March 20, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ኦማር ዶምቦያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት የትብብር መስኮችና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያና የህብረቱ ምክር ቤት የፓርላሜንታዊ ትብብር አስፈላጊ ስለመሆኑ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

በቀጣይም በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውን ከብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡