የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋርና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር በሰመራ እየተካሄደ ነው

By Hailemaryam Tegegn

March 17, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር እና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡