የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

By Hailemaryam Tegegn

March 15, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛ አመራር የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መድረኩ በክልሉ በቀጣይ ሶስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የውስጥ አንድነትን በማጠናከር የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።

በቀጣይ ጊዜያት የሚከናወኑ ተግባራት በአግባቡ በመምራትና ሁሉንም አማራጮች መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል።

የቀጣይ ሶስት ወራት ዕቅድ በክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ገብረመስቀል ጫላ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡