Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተጠናቀቀውን እና በመሰራት ላይ ያለውን የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በምሽት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በከተማዋ እየተከናወነ ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት በኮሌጅ አካባቢ በምሽት ስራ እየተሰራ መሆኑን መመልከት መቻሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በምሽት የኮሪደር ልማት እየሰሩ ያሉ ሰራተኞችን የስራ ኃላፊዎቹ ያበረታቱ ሲሆን የጎንደ ርከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው የምሽት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

የስራ ኃላፊዎች የአዞዞ-አርበኞች አደባባይ የአስፓልት ኮንክሪት የመንገድ ስራንም ጨምረው ጎብኝተዋል።

Exit mobile version