Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል ላይ በሚሠሩበት አግባብ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ባሕር ኃይሎች በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላም፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በሚኖሩ ትብብሮች ዙሪያ ምክክር መደረጉን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ፤ ትብብሩ በስልጠናና ዐቅም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም አብሮ በመሥራት ተቋማችን የጀመረውን የባሕር ኃይል ግንባታ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ውኃ ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ዝግጁነታችንን የበለጠ ለማጠናከር መክረናል ብለዋል፡፡

በጋራ ባሕር ኃይልን በሚያጠናክሩና በቀጣይ ትብብሮችን ለማመቻቸት ከውይይቱ በኋላ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

Exit mobile version