Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ብሩክ መኮንን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብሪታኒያ እና ሰሜን አየርላንድ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብሩክ መኮንን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለግርማዊ ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ አቅርበዋል።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ እና በብሪታኒያ መካከል ያለውን ታሪካዊ እና ዘላቂ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አብራርተዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ቁልፍ ጉዳዮችን መዘርዘራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የያዝነው ዓመት በሁለቱ ሀገራት ዘላቂ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት የግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊ የኢትዮጵያ ጉብኝት 60ኛ ዓመት መሆኑን ጠቅሰው፤ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ግርማዊ ንጉሱ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ መጋበዛቸውን ጠቅሰዋል።

Exit mobile version