Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በብሪክስ የግብርና የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ልዑክ በብራዚል ብራዚሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ የ2025 የብሪክስ አባል ሀገራት የግብርና የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው።

በስብሰባው በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገላጻ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተገበራችው ባሉ በርካታ ፕሮግራሞች በተለይም የስንዴ ብሔራዊ ምርትና በአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን አስረድተዋል።

በብሪክስ ማዕቀፍ ግብርና በተለይም የቤተሰብ ግብርና የትብብር መስክ ሊሆን እንደሚገባና በዚህ ረገድ ልምድ መለዋወጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሣለጥና የግብርና ግብዓቶች አቅርቦትን ማስፋፋት እንደሚገባ ገልፀዋል።

Exit mobile version