አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን አበረከቱ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለተመራው ልዑክ የእራት ግብዣ አድርገዋል።
በግብዣ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ለሩዋንዳው ኢታማዦር ሹም እና ልዑካቸው የኢትዮጵያን የባህል አልባሳትና ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እንዳበረከቱ የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር መረጃ አመልክቷል።
በተመሳሳይ ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የዓድዋ ጀግኖችን የሚያስታውስ ጋሻና ጦር የያዘ ምስልን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ኦርኬስትራ ቡድን የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎችን አቅርቧል።