Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀመንበርና የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጉብኝተዋል።

 

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሀውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

 

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version