አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ የገበታ ጨው ምርት ዓይነቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
ምርቶቹ በሚመለከተው አካል የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ሳይሰጣቸውና ጥራትና ደረጃቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ በመገኘታቸው ነው የታገዱት፡፡
ባለስልጣኑ ገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር አምስት የተለያዩ የገበታ ጨው ምርቶች የብሔራዊ የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ሳያገኙ ምልክቱን ለጥፈው ገበያ ላይ ውለው ማግኘቱን ገልጿል።
በመሆኑም ምርቶቹ ጥራታቸውና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለስልጣኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አሳስቧል።
የታገዱት ምርቶችም ሊኑ የገበታ ጨው ፣ ታሪክ የገበታ ጨው፣ ሳልት ቤይ፣ ሺማ አዮዳይዝድ ጨው እና ጂ.ኤም አይዮዳይዝድ ጨው መሆናቸው ተመላክቷል፡፡