የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያስመረቁ ነው

By Melaku Gedif

March 12, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያስመረቁ ነው፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ ጠዋት በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ድጋፍና ቁጥጥር በምስራቅ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ የተገነባውን ዘመናዊ የክፍለ ጦር የመኖሪያ ካምፕ መርቀዋል፡፡

በቀጣይም 3 ቢሊየን ብር በሆነ ወጪ በድሬዳዋ የተገነባውን የሰራዊቱ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት እና የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታልን ይመርቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡