አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) የጉሮሮ ቀዶ ሕክምና ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
የቀዶ ጥገና ሕክምናው የተከናወነው በቻይና ዥንያንግ ግዛት በሚገኝ አንድ የጉሮሮ ታካሚ ግለሰብ ላይ ነው፡፡
የጉሮሮ ቀዶ ጥገና ሕክምናው ሙሉ በሙሉ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ሮቦቶች መከናወኑን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡
ቲ ኦ አር ኤስ ኤስ የተባሉት እነዚህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሮቦቶች፤ የቀዶ ጥገናውን እስከሚያጠናቅቁ ድረስ የሻንጋይ ዩኒቨርሲቲ የዶክተሮች ቡድን ለሮቦቶቹ የሕክምና መመሪያ ሲሰጥ እና ክትትል ሲያደርግ ነበር ተብሏል፡፡
በኒቨርሲቲው የዐይን፣ የጆሮ፣ የአፍንጫ እና የጉሮሮ ስፔሻሊስት ዶክተሮች፤ በ5 ሺህ ሜትር ርቀት ላይ ለሚገኘው የዥያንግ ግዛት ታካሚ፤ ለሮቦቶች ትዕዛዝ በመስጠት የተሳካ ሕክምና ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ተሞክሮ የተሳካው ይህ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ ሕክምና፤ በቀጣይ በቻይና የጤና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
በሚኪያስ አየለ