የሀገር ውስጥ ዜና

610 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

July 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ7 ሺህ 760 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 610 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የ14 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ ማለፉንም በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በአጠቃላይም በኢትዮጵያ 253 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡

159 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 6 ሺህ 685 ሰዎች በአጠቃላይ ከቫይረሱ አግግመዋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ 66 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ለ403 ሺህ 611 ሰወች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሺህ 810 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 6 ሺህ 685 ሲያገግሙ 8 ሺህ 870 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል ተብሏል፡፡