Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተጨባጭ የልማት አቅሞችን አቀናጅቶ መጠቀም ስኬትን ያፋጥናል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተጨባጭ የልማት አቅሞችን አቀናጅቶ መጠቀም በክልሉ የታቀዱ ስራዎች እንዲሳኩ በማድረግ በኩል ፋይዳው የጎላ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የክልሉ የ2017 ግማሽ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የእቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ መድረኩ በየደረጃው ያለው አመራር የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጋራ ግንዛቤ የሚጨበጥበት እንደሆነ ገልጸዋል።

የፓርቲና አስፈፃሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም በጋራ መገምገሙ በተግባር አፈጻጸም ወቅት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version