ስፓርት

በቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ምድብ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ ተደለደለ

By Feven Bishaw

January 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል የስፔኑ ሪያል ማድሪድ እና የእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ ተገናኝተዋል።

 

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል በዛሬው ዕለት ወጥቷል።

 

የሁለቱ ሃያላን እግር ኳስ ቡድኖች ፍልሚያ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኢትሃድ የሚካሄድ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በሳንቲያጎ ቤርናባዎ ይደረጋል።

 

በሌሎች የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ብረስት ከፒኤስጂ፣ ሴልቲክ ከባየር ሙኒክ፣ ጁቬንቱስ ከፒኤስቪ፣ ፌይኖርድ ከኤስ ሚላን፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከዶርቱመንድ ተደልድለዋል።

 

ይህን የጥሎ ማለፍ የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያሸንፉ ስምንት ቡድኖች ወደ 16ቱ ምድብ ይቀላቀላሉ።

 

ሊቨርፑል፣ ባርሴሎና እና አርሰናልን ጨምሮ 8 የእግር ኳስ ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ምድብ ማለፋቸው ይታወሳል።