Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ የምድበ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሚያቸውን ሲያገኙ ማንቼስተር ሲቲ ከውድድሩ ላለመሰናበት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲዬም ክለብ ብሩጅን የሚያስተናግድ ሲሆን ከውድድሩ ላለመሰናበት እና የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታን እድል ለማግኘት ጨዋታውን ማሸነፍ ግድ ይለዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከሴልቲክ፣ ባርሴሎና ከአታላንታ፣ ባየርሊቨርኩሰን ከስፓርታ ፕራግ፣ ባየርንሙኒክ ከስሎቫን ብራቲስላቫ፣ ቦሩሺያ ዶርቱመንድ ከሻካታር ዶኔስክ፣ ብረስት ከሪያል ማድሪድ፣ ዳይናሞ ዛግሬብ ከኤሲሚላን፣ ዢሮና ከአርሰናል፣ ኢንተርሚላን ከሞናኮ፣ ጁቬንቱስ ከቤኔፊካ፣ ሊል ከፌይኑርድ፣ ፒኤስቪ ከሊቨርፑል፣ ሬድ ቡል ሳልዝበርግ ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከቦሎኛ፣ ስትሩም ግራዝ ከአርቢ ሌይብዢግ፣ ስቱትጋርት ከፒኤስጂ እንዲሁም ያንግ ቦይስ ከሬድ ስታር ቤልግሬድ በሚያድርጉት ጨዋታ የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የምድብ ጨዋታዎች ፍጻሚያቸውን ያገኛሉ፡፡

በዚህም መሰርት ከ1-8 ደረጃን ይዘው የሚጨርሱ ቡድኖች በቀጥታ 16ቱን ሲቀላቀሉ ከ9-24 ደረጃን በመያዝ የሚያጠናቅቁ ቡድኖች የጥሎ ማላፍ ጨዋታን በማድረግ አሸናፊዎቹ 16ቱን ይቀላቀሉ።

ቀሪዎቹ ከ25 – 36ተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ከውድድሩ የሚሰናበቱ ይሆናል፡፡

Exit mobile version