ስፓርት

ቤልጂዬማዊው ተጨዋች ኔይንጎላን በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Feven Bishaw

January 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 19 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤልጂዬማዊው ተጨዋች ራጃ ኔይንጎላን በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡

የ36 ዓመቱ የቀድሞ የኢንተርሚላን እና የሮማ ተጫዋች ራጃ ኔይንጎላን ኮኬይን በመባል የሚታወቀውን አደንዛዥ እጽ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አውሮፓ በአንትረፕ ወደብ በኩል ሲያዘዋውር መገኘቱ ተነግሯል፡፡

የአማካኝ ስፍራ ተጨዋቹ ራጃ ኔይንጎላን ባሁኑ ሰዓት በቤልጂዬም ሁለተኛ እርከን በሚሳተፈው ሎከርን ለተሰኘ ክለብ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ራጃ ኔይንጎላን በፈረንጆቹ 2009 እና 2018 ለቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን 30 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ተጫውቷል፡፡