የሀገር ውስጥ ዜና

የምስራቅ ዕዝ ኮር የሰላም አማራጭ ባልተቀበሉ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

By Mikias Ayele

January 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ ዕዝ ኮር ሰሞኑን ባደረገው ስምሪት የሰላም አማራጭ ባልተቀበሉ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ።

በስምሪቱ በርካቶችን ሙት በማድረግ ትጥቆችንና የሎጂስቲክ ቁሳቁሶችን መማረክ መቻሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ አመልክቷል።

ታጣቂዎቹ ዋሽራ በተባለው አካባቢ በአራት አቅጣጫ ትንኮሳ ቢሞክሩም ሰራዊቱ ባደረገው ፀረ-ማጥቃት እርምጃ የመጣው ታጣቂ መደምሰስ መቻሉን የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አለሜ ታደለ ገልፀዋል፡፡

ኮሩ በሰሜን ጎጃም ዞን እና ባህር ዳር ዙሪያ ግንደሎሚ፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዋሽራ ቀበሌ ባደረገው ስምሪት 41 የሰላም አማራጭ ያልተቀበሉ ታጣቂዎችን በመደምሰስ፣ 30 ክላሽንኮቭ፣ 21 ኋላ ቀር መሳሪያ፣ 2 የእጅ ቦምብ፣ 5 ትጥቅና የተለያዩ ወታደራዊ አልባሳት መማረክ መቻሉ ተነግሯል።