የሀገር ውስጥ ዜና

ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

July 25, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡

በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም እንደሚገመግምም ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህ ባለፈም የ2013ን በጀት ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ጠቁመዋል።

እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ ቃለ ጉባኤ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የክልሉ የውሃና ፍሳሽ አዲስ ደንብ ማጽደቅም የጉባኤው አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራሮች ቦታ ሹመት ያጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡