አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ያለበትን ደረጃ ገምግመዋል፡፡
በግምገማው ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ እና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት÷በተያዘው እቅዱ መሰረት ሥራዎች በላቀ ፍጥነት እንዲሰሩ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮሪዳር ልማት ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለታለመለት አላማ እንዲውሉም በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡