የሀገር ውስጥ ዜና

የኢራን ፓርላማ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ

By yeshambel Mihert

January 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባቀር ቃሊባፍ(ዶ/ር) የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ ለልዑካን ቡድኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት አፈ ጉባኤ ታገሰ፤ ኢትዮጵያና ኢራን ተመሳሳይ ባህልና ሀይማኖት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት መሆናቸውን ገልፀው፤ የሀገራቱ ወዳጅነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ አረጋግጠዋል።

የኢራን ፓርላማ ልዑክ ቡድን አባላት በቆይታቸው የተለያዩ ጉብኝቶችን እንደሚያደርጉና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ እና ከሌሎች የመንግስት ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ አመልክቷል።