አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለጥምቀት በዓል የበርካታ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የጃን ሜዳ አካባቢ ማጽዳታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በጽዳት መርሐ-ግብሩ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተወካዮች እና የአካባቢው ነዎሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የጽዳት መርሐ ግብሩ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የጥምቀት በዓል አብሮነትን፣ አንድነትንና ወድማማችነትን የሚያጠናክርና በርካታ የውጭ ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡