Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኬኒያ እስርቤቶች የነበሩ 346 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕገ-ወጥ ደላሎች ተታልለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሞክሩ በኬኒያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 346 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

እነዚህ ወገኖች ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኬኒያ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እና ከኬኒያ ኢሚግሬሽን ቢሮ ጋር በትብብር ባከናወነው ሥራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚያስችሉ አሠራሮች ከተከናወኑ በኋላም በዛሬው ዕለት በሞያሌ ድንበር ወደ ኢትዮጵጵያ እንዲመለሱ መደረጉን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version