Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት እያደረገች ያለውን ጥረት ቻይና ትደግፋለች – አምባሳደር ቸን ሃይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት እያደረገች ያለውን ጥረት መንግስታቸው እንደሚደግፍ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ገለጹ።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ልዩ መልክአምድራዊ እና ፖሊቲካዊ ስፍራ እንዳላት የገለጹት አምባሳደሩ ሀገራትን በኢኮኖሚ በማስተሳሰር እና ለአፍሪካ አህጉር መግቢያ በመሆን እየተወጣች ያለችውን ሚና ለማጠናከር የባህር በር ያስፈልጋታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን የየብስ ክፍል ከባህር በር እንዲሁም ከውቅያኖሶች ጋር ለማገናኘት እያደረገ ያለውን ሰላማዊ ጥረት ቻይና ትደግፋለች ሲሉም አምባሳደር ቸን ሃይ ከፋና ዲጂታል ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ቻይና የብሪክስ አባላት እንደሆመናቸው ስብስቡን ለተሻለ ትብብር እና ተጠቃሚነት እንደሚያውሉት ያላቸውንም እምነት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ ብቻ ሳትሆን የክፍለ ዓለሙ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ እምብርት ነች ያሉት አምባሳደሩ÷ ሃገሪቱ ለቀጣናው ሰላም እና ብልጽግና መረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት መንግስታቸው እንደሚደግፍ ጨምረው ገልጸዋል።

በወንደሰን አረጋኸኝ

Exit mobile version