የሀገር ውስጥ ዜና

የፋሲለደስ እድሳትና የጎንደር ኮሪደር ልማት ሥራ እድገት እጅግ አበረታች ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

January 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡

በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይም በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል፡፡