Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

16ኛው የአማራ ክልል የባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 16ኛው የአማራ ክልል የባህል ፌስቲቫል “ድንቅ ምድር ድንቅ ባህል” በሚል መሪ ሐሳብ በጎንደር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ ከክልሉ 13 ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የባህል አምባሰደሮች፣ ከትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና አፋር ክልሎች የተጋበዙ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡

በፌስቲቫሉ የቴአትር እና የሙዚቃ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የተገለጸ ሲሆን÷ ለቀደምት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችም እውቅና ይሰጣል ተብሏል፡፡

ፌስቲቫሉ ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማነቃቃትና የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማጠናከር ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር መልካሙ አዳሙ ተናግረዋል።

በፌስቲቫሉ የመክፈቻ መርሐ-ግብር ላይ የክልል እና በየደረጃው የሚገኙ የዞን እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በበላይነህ ዘላለም

Exit mobile version