የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ብሪታኒያ ትስስራቸውን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለፁ

By Meseret Awoke

January 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ብሪታኒያ በፓርላማቻቸው መካከል ያለውን ትብብር በማሳደግ ትስስራቸውን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

በብሪታኒያና በሰሜን አየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን ከእንግሊዝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሊንሳይ ሆይሌ ጋር መክረዋል፡፡

በምክክራቸውም ወቅት አምባሳደሩ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ስላለው የኢኮኖሚ ሪፎርም አብራርተውላቸዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የነበረውን ታሪካዊና ወንድማማችነት ግንኙነትም በዚህ ወቅት አንስተዋል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር፣ በሀገራቱ ፓርላማዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግና ትስስራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ሁለቱም ወገኖች ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።