Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በርዕደ መሬቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በርዕደ መሬቱ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለፁ።

አቶ አወል አርባ ከአዋሽ ፈንታሌና ዱለሳ ወረዳዎች በርዕደ መሬቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖችን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት÷በርዕደ መሬቱ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጨምሮ፣ የሃገር ሸማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሥነ-ምድር ተመራማሪዎች የሚያስተላለፉትን መልዕክት መቀበል እንደሚገባም ተናግረዋል።

አቶ አወል በመጠለያ ጣቢያ በመገኘት የተፈናቀሉትን ወገኖች ያበረታቱ ሲሆን÷የምግብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version