አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ ከ160 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ስደተኞችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡