Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለ340 የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበበ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ340 የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላለፉ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ለመተግበር የፖሊሶችን ካምፕ በጎበኙበት ወቅት የሰራዊቱ አባላት ካምፕ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እጅግ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ለነዋሪዎች እንዳደረግነዉ ሁሉ ቤተሰብ ላላቸው 340 የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላልፈናል ብለዋል።

ፖሊስ ቅድሚያ ለህዝብ በማለት ለሀገር ደህንነት ዋጋ እየከፈለ የሚያገለግል እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ለሰራዊቱ ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖረዉ ከተቋሞቻቸዉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምንሰራ ይሆናል ነው ያሉት::

Exit mobile version