Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ቀብር ሥነ-ሥርዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡

የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ አስከሬን ለገ ጣፎ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።

በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው የአስከሬን ሽኝት መርሐ-ግብርም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት፥አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ቅድሚያ ለሀገርና ትውልድ በመስጠት በታማኝነትና በታላቅ ስብዕና ማገልገልን ያስተማሩ ሰው እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በ94 ዓመታቸው ታሕሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን ፥ 11 የልጅ ልጆችንም አይተዋል፡፡

Exit mobile version